አምሳለ አበራ ሎዉ ፒኤልኤልሲ በቤልጲዉ የሚገኝ በኢሚግሬሽን ሕግ ላይ ያተኮረ አጠቃላይ የጥብቅና አገልግሎት የሚሰጥ የሕግ ድርጅት ነው። የእኛ ቢሮ በኢሚግሬሽን ፍርድ ቤት የፍርድ ክርክር ፣ በጥገኝነት ማመልከቻቸው፣ በቤተሰብ ላይ የተመረኮዘ ኢሚግሬሽን፣ የንግድ ሥራ የኢሚግሬሽን ፍላጎቶች ወይም በማናቸውም ከኢሚግሬሽን ጋር በተገናኙ ጉዳዮች ላይ ደንበኞችን ወክሎ  ጥብቅና ይቆማል። የእኛ ደንበኞች ውስብስብ በሆነው የአሜሪካ የኢሚግሬሽን ሕግ ላይ የእኛ በሙያው ጥልቅ ክህሎት ያላቸው ልምድ ያካበቱ የቡድን አባላቶቻችን ጋር አብረው እንደሚሰሩ ስለሚያውቁ ቀለል ያለ ስሜት ይሰማቸዋል።

የእኛ ቢሮ በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞ እና በፈረንሣይኛ አገልግሎቶች ይሰጣል። በተጨማሪ በቅድሚያ ሲጠየቅ በሌሎች ቋንቋዎች አስተርጓሚዎችን ማግኘት ይቻላል።

ስለ ጠበቃ አምሳለ አበራ

አምሳለ አበራ  የ አምሳለ አበራ ሎዉ ፒኤልኤልሲ ድርጅት መሥራች ጠበቃ ናቸው። እራሳቸው ለአሜሪካን ሃገር መጤ እንደመሆናቸዉ መጠን፣ የአሜሪካ የኢሚግሬሽን ሕጎች ምን ያክል የተወሳሰቡ እንደሆኑ በሚገባ ይረዳሉ፣ በመሆኑም ለእሳቸው ደንበኞች በአገር አቀፍ ደረጃ ልዩ ፣ ፍቅርና ርህራሄ የተሞላበት አገልግሎት ለመስጠት ማናቸውንም ጥረት ሁሉ ያደርጋሉ። ጠበቃ አምሳለ ደንበኞችን በጥገኝኘት ላይ የተመረኮዘ ማመልከቻቸው፣ ቤተሰብ ላይ የተመረኮዘ የኢሚግሬሽን ጥያቄያቸው ላይ ፣የንግድ ጉዳይ ኢሚግሬሽን ጉዳዮች፣ ከሀገር ማስወጣትን ለመከላከል እንዲሁም ማናቸዉንም የኢሚግሬሽን ጉዳዮች በተመለከተ አገልግሎት ይሰጣሉ።

ጠበቃ አምሳለ በ ኢሚግሬሽን ህግ ዙሪያ የብዙ አመት ልምድ ያካበቱ ሲሆን ከተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር (United Nations High Commissioner for refugees)፣ ጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ (Johns Hopkins University) እና ከ  ኖርዝ ዌስት ኢሚግራንት ራይት ፕሮጀክት(North West Immigrants’ Rights Project) ጋር አብረው ሰርተዋል። ጠበቃ አምሳለ ከ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የህግ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን፣ የማስተርስ ዲግራቸውን በኮስታሪካ ከሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ዩኒቨርስቲ (United Nations Mandated University)፣ እና የሕግ የማስተር ዲግሪያቸውን በሲያትል ከሚገኘው የዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ (University of Washington) አግኝተዋል። ጠበቃ አምሳለ በዓለም አቀፍ ሕግ ላይ ያላቸው ልዩ ልምድና ተሞክሮ፣ እንዲሁም በአምስት አህጎሮች እንደመኖራቸው፣ መማራቸው እና መጓዛቸው፣ ደንበኞቻቸው ሊኖራቸው የሚችለውን የባሕል እና የፖለቲካ ልዩነት እንዲገነዘቡ እና በተለያዩ መጠነ ሰፊ የኢሚግሬሽን ሕጎች ዙሪያ ጥብቅና እንዲቆሙላቸው ያግዛቸዋል።

የባር ፈቃድ

ዋሽንግተን

አባልነት

የአሜሪካ ኢሚግሬሽን ጠበቆች ማህበር (American Immigration Lawyers Association)

የኪንግ ካውንቲ የባር ማህበር (King County Bar Association)

የኢስት ኪንግ ካውንቲ ባር ማህበር (East King County Bar Association)

የመገኛ አድራሻ መረጃ

የቢሮ አድራሻ፦14205 SE 36th St, Suite 100 Bellevue, WA 98006

ስልክ፦ 206-734-7614

ፋክስ፦ +1 206-274-4836

ኢሜይል፦ amsale@aberralaw.com

አገልግሎቶች

የ አምሳለ አበራ  የሕግ ቢሮ በመላ ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ለሚገኙ ደንበኞች የሚከተሉትን ጨምሮ የኢሚግሬሽን ሕግ አገልግሎቶች ላይ ምክር እና የጥብቅና አገልግሎቶችን ይሰጣል፦

ጥገኝነት

የ አምሳለ አበራ  የሕግ ቢሮ በዩኤስሲአኤስ  እና በኢሚግሬሽን ፍርድ ቤት ያሉ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ያግዛል። በዘር ሐረጋቸው፣ በኃይማኖታቸው፣ በፖለቲካ አስተሳሰባቸው፣ ዜግነታቸው ወይም ባላቸው የማኅበራዊ ቡድን አባልነት የተነሳ ስቃይ የደረሰባቸው ወይም ወደፊት ስቃይ ሊደርስባቸው እንደሚችል በተጨባጭ ማስረጃ ላይ የተመረኮዘ ፍራቻ ላላቸው የጥገኝነት ጠያቂዎችን በአሜሪካን ሃገር የጥገኝነት ፈቃድ እንዲያገኙ በማገዝ የበርካታ ዓመታት ልምድ አለን።

የቤተሰብ ቪዛዎች

ለአሜሪካ ዜግነት/ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ላላቸው ነዋሪዎች የቅርብ ዘመድ ወይም የቤተሰብ አባል ግሪን ካርድ

 ከዚህም በተጨማሪ የሚከተሉትን የቤተሰብ ምድብ ግሪን ካርድ፦

ኬ-ቪዛ የአሜሪካ ዜግነት ላለው እጮኛ እና አብረው ለሚመጡ ዕድሜያቸው ለአካለ መጠን ያልደረሰ ሕጻናት (ኬ-1 እና ኬ -2 ቪዛዎች) 

የአሜሪካ ዜግነት ያለው ወይም ህጋዊ ቋሚ ነዋሪ የሆነ ሰው ልጅ ወይንም ባለቤት ሆነው የቤት ውስጥ ጥቃት ለደረሰባቸዉ አገልግሎት እንሰጣለን

የንግድ ቪዛዎች

ዜግነት

የቆንሲል ስራ ማስኬድ

የኢሚግሬሽን ፍርድ ቤት እና የፍርድ ክርክር

ምክክር

ከጠበቃ ጋር የሃያ ደቂቃ ነጻ ምክክር ለማግኘት፣ ወደ  206-734-7614 ይደውሉ የምሽት እና በሳምንት  መጨረሻ ቅዳሜና እሁድ ጭምር የምክር አገልግሎቶችን እንሰጣለን።

ክፍያዎች

የዴቢት፣ የክሬዲት ካርድዎን ወይም የእርስዎን Paypal በመጠቀም ለእኛ አገልግሎቶች መክፈል ይችላሉ። ይህን የክፍያ አማራጭ ለመጠቀም የሚሰራ የኢሜይል አድራሻ ሊኖርዎት ይገባል።

ከዚህ በታች ያለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ እና ወደ የPaypal የድር ጣቢያ ይወሰዳሉ።

እየከፈሉ ያሉበትን አገልግሎት ዝርዝር (የመጀመሪያ የምክር አገልግሎት፣ ሙሉ ክፍያ ወይም ቀስ በቀስ የሚደረግ ክፍያ) እና እየከፈሉ ያሉትን ገንዘብ መጠን ያስገቡ። የክፍያ ስልቱን ይምረጡ፣ የሚጠየቀውን መረጃ ያስገቡ፣ እና ክፍያዎን ለመፈጸም "Pay Now" የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ።